O A E

info@dvlca.gov.et

0116672315/0116672329

7766

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን

Addis Ababa Driver and vehicle licensing and control Authority

ማገልገል ክብር ነው!
የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን በአዲስ አበባ ከተማ አስታዳደር ስር ያሉ አስፈፃሚ አካላትን እንደ አዲስ ለማዋቀር በወጣው አዋጅ 43/2007 መሰረት ተጠሪነቱ ለአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ሆኖ በከተማ አስተዳደር የሚገኙ የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ተቋማትን በማደራጀት፣ ክትትልና ቁጥጥር አግባብን በማጠናከር አፈፃፀማቸውን በማሳደግ የአገልግሎት አሰጣጡን ጥናትና ምርምር በማካሄድ ውጤታማ የአሽከርካሪ ተሸከርካሪ ቁጥጥር ብቃት ማረጋገጥ ዋነኛ የባለስልጣኑ ተልዕኮ እንዲኖረው ተደርጎ የተቋቋመ ሲሆን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱም በአዋጁ የተሰጡትን ተግባራትና ሃላፊነቶች ተደራሽ እና ተገቢ በሆነ መልኩ ለመወጣት በማዕከል እና በአስራ ሁለት ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ከ2008 ዓ/ም ጀምሮ እየሰጠ ያለ ሲሆን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከተማ አስተዳደሩ በ2016 ዓ/ም ሪፎርም እንዲያደርጉ ከተመረጡ 16 ተቋማት መካከል አንዱ በመሆኑ የተሰጡትን ተግባርና ሃላፊነቶች በተሻለ መንገድ ለመወጣት እንዲያስችለው የሰው ሃይል እና የአደረጃጀት ለውጥ በማድረግ በአዲስ መልክ ተደራጅቷል፡፡ እኛም እናንተን ዝቅ ብለን ስናገለግል ታላቅ ደስታና ክብር ይሰማናል፡፡

Vision(ራዕይ)

በከተማችን ብቁ አሽከርካሪና ብቃቱ የተረጋገጠ ተሸከርካሪ ኢንዲኖር በማድረግ በ2023 ዓ.ም የሀገራችን ሞዴል አገልግሎት ሰጪ ተቋም ሆኖ ማየት ነው

Mission

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ተቋማትን በማደራጀት፣ የክትትልና ድገፍ እንዱሁም የቁጥጥርና የግምገማ አግባብን በማጠናከር፣ አፈፃፀማቸዉን በማሳደግ፤ አገልግሎት አሰጣጡንና የመረጃ አያያዝ ስርዓትን በማዘመን እንዲሁም ጥናትና የዓሰራር ማሻሻያን በማካሄድ ዉጤታማ የአሽከርካሪና ተሸከርካሪ ፈቃድና ብቃት ማረጋገጥ ነዉ፡፡

Core Values

  1. 1. ቅንነት (Integrity)
  2. 2. ግልፀኝነት (Transparency)
  3. 3. ተጠያቂነት (Accountability)
  4. 4. አለማዳላት (Imparciality)
  5. 5. ቅልጥፍናና ውጤታማነት (Efficiency & Effectiveness)
  6. 6. ቅንጅትና ትብብር (Integration and Collaboration)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ተግባር ኃላፊነት


1
ማሰልጠኛ ተቋማት ብቃት ፈቃድ መስጠት
  • አግባብ ባለው ህግ መሰረት ተሽከርካሪዎችን ይመዘግባል
  • አግባብ ባለው ህግ መሰረት ተሽከርካሪዎችን ይመዘግባል፣ የስም ዝውውር፣ የእዳና እገዳ አገልገሎት ይሰጣል
2
ለአሽከርካሪ አሰልጣኞች ማስተማሪያ ፈቃድ
  • ለአሽከርካሪ አሰልጣኞች ማስተማሪያ ፈቃድ መስጠት
  • ለአሽከርካሪ አሰልጣኞች ማስተማሪያ ፈቃድ ማደስ
  • ለአሽከርካሪ አሰልጣኞች ማስተማሪያ ፈቃድ ለውጥ መስጠት
3
ለማሰልጠኛ ተቋማት የማለማመጃ ተሽከርካሪ ጭማሪና ቅያሪ ፈቃድ መስጠት
  • የማሰልጠኛ ተቋማት ተመሳሳይ ካታጎሪ ጥያቄ ቅያሬ መስጠት
  • የማሰልጠኛ ተቋማት ተመሳሳይ ያልሆነ ካታጎሪ ጥያቄ ቅያሬ መስጠት
  • የማሰልጠኛ ተቋማት ተሽከርካሪ ጭማሬ መስጠት
4
በታክሲ አገልግሎት የተመዘገቡ ተሽከርካሪዎችን ለማሽከርከር የሚያስችለውን ስልጠና አገልግሎት መስጠት
  • የታክሲ ልዩ ስልጠና ሰነድ ገቢ መቀበል
  • የታክሲ ልዩ ስልጠና ሰነድ ወጪ ማድረግ
5
የእጩ አሽከርካሪዎች የምዘና ቀጠሮ መስጠት
  • የእጩ አሽከርካሪዎች የንድፈ ሃሳብ የምዘና ቀጠሮ መስጠት
  • የእጩ አሽከርካሪዎች የተግባር የምዘና ቀጠሮ መስጠት
6
የእጩ አሽከርካሪዎች የምዘና ቀጠሮ
  • የንድፈ ሃሳብ የምዘና ቀጠሮ መስጠት
  • የተግባር የምዘና ቀጠሮ መስጠት

በ11ዱ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች የሚሰጡ አገልግሎቶች



1. የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ እድሳት አገልግሎት መስጠት
2. ወደ ውጪ ሃገር ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ትክክለኛነት ማረጋገጫ መስጠት (ኢንተርናሽናል)
3. የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ምትክ መስጠት
4. ከአዲስ አበባ ወደ ክልል ፋይል ዝውውር አገልግሎት መስጠት
5. የልዩነት ስልጠና ለሚወስዱ አሽከርካሪዎች መረጃዎችን መስጠት
6. በታክሲ አገልግሎት የተመዘገቡ ተሽከርካሪዎችን ለማሽከርከር የሚያስችለውን ብቃት ማረጋገጫ መስጠት
7. የንድፈ ሃሳብ ምዘና መስጠት
8. የንድፈ ሃሳብ ምዘና ለወደቁ ተፈታኞች ድጋሚ ቀጠሮ መስጠት
9. የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ እግድ ማንሳት
10. የአሽከርካሪ መረጃ መስጠት

የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን
ደሳለኝ ተረፈ (ኢንጂነር)
ዋና ስራ አስኪያጅ

DVLCA Main Roles


The Driver's Vehicle Permit Control Authority under the Addis Ababa City Administration provides a range of services aimed at regulating and monitoring vehicle permits, ensuring safety, and maintaining compliance with transportation laws


Issuance of Driver's Licenses
Vehicle Registration and Permits
Inspection Services
Permit Enforcement
Data Management and Record Keeping
Public Awareness and Training
Complaint and Inquiry Services

የባለስልጣኑ ተገልጋዮች

1. አሽከርካሪዎች
2. የተሽከርካሪ ባለንብረቶች
3. የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት
4. የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ፈላጊዎች /እጩ አሽከርካሪዎች/
5. የተሽከርካሪ ምርመራ ተቋማት
6. የተሽከርካሪ ጥገና ተቋማት
7. ባንኮችና ኢንሹራንሶች

Clients
Empowering Addis Ababa: Enhancing Urban Life Through Vehicle Permit Regulation

Empowering Addis Ababa: Enhancing Urban Life Through Vehicle Permit Regulation

In General, the services provided by the Driver's Vehicle Permit Control Authority contribute significantly to Addis Ababa's transformation into a safer, more organized, and environmentally conscious urban center. These benefits align with the city's long-term goals of sustainability, economic development, and enhanced quality of life. The Driver's Vehicle Permit Control Authority in Addis Ababa offers several advantages to the city, contributing to its development, safety, and efficiency.

Contact For Any Comments

ማገልገል ክብር ነው!!!

Our Address

22 ወደ መገናኛ መንገድ መክሊት ህንፃ

info@dvlca.gov.et

0116672315/0116672329

Toll Free 7766

Follow Us

© 2025 Addis Ababa Driver and vehicle licensing and Control Authority. All rights reserved.