info@dvlca.gov.et

0116672315/0116672329/7766

About Us

Home About

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን

Addis Ababa Driver and vehicle licensing and control Autority

ማገልገል ክብር ነው!
የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን በአዲስ አበባ ከተማ አስታዳደር ስር ያሉ አስፈፃሚ አካላትን እንደ አዲስ ለማዋቀር በወጣው አዋጅ 43/2007 መሰረት ተጠሪነቱ ለአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ሆኖ በከተማ አስተዳደር የሚገኙ የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ተቋማትን በማደራጀት፣ ክትትልና ቁጥጥር አግባብን በማጠናከር አፈፃፀማቸውን በማሳደግ የአገልግሎት አሰጣጡን ጥናትና ምርምር በማካሄድ ውጤታማ የአሽከርካሪ ተሸከርካሪ ቁጥጥር ብቃት ማረጋገጥ ዋነኛ የባለስልጣኑ ተልዕኮ እንዲኖረው ተደርጎ የተቋቋመ ሲሆን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱም በአዋጁ የተሰጡትን ተግባራትና ሃላፊነቶች ተደራሽ እና ተገቢ በሆነ መልኩ ለመወጣት በማዕከል እና በአስራ ሁለት ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ከ2008 ዓ/ም ጀምሮ እየሰጠ ያለ ሲሆን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከተማ አስተዳደሩ በ2016 ዓ/ም ሪፎርም እንዲያደርጉ ከተመረጡ 16 ተቋማት መካከል አንዱ በመሆኑ የተሰጡትን ተግባርና ሃላፊነቶች በተሻለ መንገድ ለመወጣት እንዲያስችለው የሰው ሃይል እና የአደረጃጀት ለውጥ በማድረግ በአዲስ መልክ ተደራጅቷል፡፡ እኛም እናንተን ዝቅ ብለን ስናገለግል ታላቅ ደስታና ክብር ይሰማናል፡፡ ባለስልጣን መስሪያቤቱ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በተቀመጡት ቅድመ ሁኔታዎችና ስታንዳርዶች ያለምንም ችግር የማግኘት መብት ያላችሁ ሲሆን በዚህ ሰነድ የተቀመጡትን አገልግሎቶች ለማግኘት ምንም እንቅፋት ቢገጥማችሁ ችግራችሁን ለመፍታትና ችግሩን የፈጠሩ አካላትን በአሰራርና በህግ አግባብ ለመጠየቅ ዝግጁ መሆናችንን እንዲሁም ሁልጊዜም እናንተን ለማገልገል በራችን ክፍት መሆኑን ልገልጽ እንወዳለሁ፡፡

Vision(ራዕይ)

በከተማችን ብቁ አሽከርካሪና ብቃቱ የተረጋገጠ ተሸከርካሪ ኢንዲኖር በማድረግ በ2023 ዓ.ም የሀገራችን ሞዴል አገልግሎት ሰጪ ተቋም ሆኖ ማየት ነው

Mission

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ተቋማትን በማደራጀት፣ የክትትልና ድገፍ እንዱሁም የቁጥጥርና የግምገማ አግባብን በማጠናከር፣ አፈፃፀማቸዉን በማሳደግ፤ አገልግሎት አሰጣጡንና የመረጃ አያያዝ ስርዓትን በማዘመን እንዲሁም ጥናትና የዓሰራር ማሻሻያን በማካሄድ ዉጤታማ የአሽከርካሪና ተሸከርካሪ ፈቃድና ብቃት ማረጋገጥ ነዉ፡፡

Core Values

1. ቅንነት (Integrity)
2. ግልፀኝነት (Transparency)
3. ተጠያቂነት (Accountability)
4. አለማዳላት (Imparciality)
5. ቅልጥፍናና ውጤታማነት (Efficiency & Effectiveness)
6. ቅንጅትና ትብብር (Integration and Collaboration)

Our Galleries


dlvca

dlvca

dlvca

dlvca

dlvca

dlvca

ማገልገል ክብር ነው!!!

Our Address

22 ወደ መገናኛ መንገድ መክሊት ህንፃ

info@dvlca.gov.et

0116672315/0116672329

Toll Free 7766

Follow Us

© 2025 Addis Ababa Driver and vehicle licensing and Control Autority. All rights reserved.